የሚፈለጉ
ሃፊዝ አብዱል ራማን ማኪ
አይማን አልዘዋሃሪ
እስከ 25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ
የትውልድ ቦታ : ግብፅ
ፀጉር : ቡናማ/ጥቁር
አይኖች : ጥቁር
ፆታ : ወንድ
ብሔር : ግብፃዊ
ተለዋጭ መጠሪያ : አቡ መሀመድ፣ አቡ ፋጢማ፣ መሀመድ ኢብራሂም፣ አቡ አብደላ፣ አቡ አልሙኢዝ፣ ዶክተር መምህር፣ ኑር፣ ኡስታዝ፣ አቡ መሀመድ፣ አቡ መሀመድ ኑር አልዲን፣ አብደል ሙአዝ፣ ዶ/ር አይማን አልዘዋሃሪ
አይማን አልዘዋሃሪ፣ ሀኪምና የግብፁ ኢስላሚክ ጅሃድ መስራች ነው፡፡ ይህ ድርጅት አለማዊው የግብፅ መንግስት በመቃወም መንግስቱን በሀይል ለማስወገድ ይጥራል፡፡ አልዘዋሃሪ የኡሳማ ቢን ላደን አማካሪና ሐኪም ነበር ተብሎ ይታመናል:: ታንዛኒያና ኬንያ ውስጥ በሚገኙት የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ነሀሴ 7, 1998 ለተፈፀሙት የቦንብ ጥቃቶች ላይ በነበረው ሚና ተፈላጊ ነው፡፡
ከላይ በሥም የተጠቀስው ግለሰብ በሚከተሉት ክሶች ተወንጅሏል:
ከአሜሪካ ውጭ በሚገኙ ቦታዎች በአሜሪካ ዜጎች ላይ ግድያ መፈጽም፣ ከአሜሪካ ውጭ በሚገኙ ቦታዎች በአሜሪካ ዜጎች ላይ ግድያ ለመፈጸም ማሴር፣ በፌደራል ተቋማት ላይ ሞትን ያስከተለ ጥቃት ማካሄድ
አይማን አልዘዋሃሪ፣ ፋዙል አብዱላህ መሀመድ፣ ፋሂድ መሀሙድ አሊ ሰላም፣ ሸህ አህመድ ሳሊም ስዌዳን፣ አብዱላህ አህመድ አብዱላህ፣ ሳይፍ አል አደል፣ አናስ አል ሊቢ፣ አህመድ መሀመድ ሃሚድ አሊ፣ አሁን ሟቹ ኡሳማ ቢን ላደን እና በቁጥጥር ስር የዋሉ ሌሎች ህዳር 7፣1998 ኬንያና ታንዛኒያ ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ለደረሱት የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂዎች ናቸው ተብሎ ይታመናል፡፡ በኤምባሲዎቹ ላይ በደረሱት የቦንብ ጥቃቶች 224 ሰላማዊ ሠዎች ሲገደሉ ከ5,000 በላይ የሆኑ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ እነዚህ አሸባሪዎች የአለም አቀፍ አሸባሪ የመረብ ትስስር የሆነው ድርጅት የአልቃኢዳ አባላት ናቸው ተብሎ ይታመናል፡፡
Click here to listen to a Public Service Announcement about this terrorist

