የተከፈሉ ወሮታዎች
2. ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም የአለምአቀፍ ሽብር ጥቃቶችን ለማክሸፍ ያስቻሉ ወይም በቀድሞ የሽብር ጥቃቶች ላይ የተሳተፉ ሰዎችን ወደፍትህ ለማቅረብ የረዱ መረጃዎችን ለሰጡ ከ60 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የበለጠ ወሮታ ከፍሏል፡፡
በነዚህ መረጃዎች መነሻነትም ከብዙዎች ሌሎች የሚከተሉት ግለሰቦች ወደፍትህ እንዲቀርቡ የደርጓል፡፡:
ዑዴ ሁሴን
ቁሳይ ሁሴን
ራምዚ አህመድ ዩሴፍ
ሚር አይማል ካንሲ
ሃምሲራጂ ማሩሲ ሳሊ
ቶቲንግ ክራፍት ሃኖ
ሙህሲን ከድር አልካፋጂ
ካሚስ ሲርሃን አልመሃመድ
መሀመድ ዝማም አብድራዛቅ አልሳዱን
ካዳፊ ጃንጃላኒ
አቡ ሶ ለይማን
ኤድጋር ናቫሮ
መረጃዎን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ልበ ሙሉ ግለሰቦችም የሽብርተኝነት ጥቃቶችን በመከላከልና በማስቀረት ረገድ የራሳቸውን እርዳታ አበርክተዋል፡፡:
- የፋርስ ባህረ ሰላጤ ጦርነት በሚካሄድበት ወቅት ከምስራቅ ኤሰያ አገር የተገኘ ጎበዝ መረጃ አቅራቢ ግለሰብ ስለታቀዱ ተከታታይ የሽብር ጥቃቶች መረጃ ሰጥቷል፡፡ አሸባሪዎቹ በወቅቱ ጥቃት ሊፈጽሙባቸው ያቀዷቸውን ኢላማዎች ለይተው በማስቀመጥ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያዎችን የእጅ ቦምቦችንና ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን አዘጋጅተው ነበር፡፡ ከታቀዱት ጥቃቶች መካከል የመጀመሪያው ከመድረሱ ጊዜ ከ48 ሰዓት በፊት ይህ መረጃ ሰጭ የአሸባሪዎቹን እቅድ ለማኮላሸት በጣም ወሳኝ የሆነውን መረጃ ሰጥቷል፡፡ ጥቃቱ ከሽፎ መረጃ ሰጪው ወጣት ከፍተኛ ወሮታ ተለግሶለት ቤተሰቡ ደህንነቱ ወደ ተረጋገጠ ቦታ እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ ግለሰቡ ይህንን መረጃ በመስጠቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ከሞት አትርፏል፡፡.
- በሌላ ሁኔታ ደግሞ፣ አንዲት ወጣት ሴት የመንገደኞች ማጓጓዣ አውሮፕላንን በመጥለፍ በውስጡ የነበሩ ተጓዦችን በአሰቃቂ ሁኔታ ስለ ደበደቡ ሰዎች መረጃ ይዛ መጣች፡፡ " ፍትህ ተፈጻሚ መሆን አለበት" የሚል ጠንካራ ስሜት እንዳደረባት ተናግራለች:: የጠላፊዎቹ መሪ ወደ አሜሪካ እንዲመለስ ተደርጎ በቀረበበት የአውሮፕላን ጠለፋ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ እስር ቤት ሊገባ ችሏል፡፡ ወጣቷ ሴት ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ላደረገችው ጥረት ወሮታዋን አግኝታለች፡፡.
- በአንድ የውጭ ሀገር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪ የሆነች ሌላ ወጣት ሴት በአንድ የአሜሪካ ዲፕሎማት ላይ በጭካኔ ስለ ተፈፀመ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ምስክርነቷን ሰጥታለች፡፡ እሷ በሰጠችው መረጃ ምክንያትም በሁለት ጥቃት ፈጻሚዎች ላይ ፍ/ቤት የእድሜ ልክ እስር ሊወስንባቸው ችሏል፡፡ ተማሪዋና ቤተሰቧ ደህንነቱ አስተማማኝ ወደሆነ ቦታ እንዲዛወሩ ተደርገው ተማሪዋ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ወሮታ ተሰጥቷታል፡፡.
